በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት ወራሪ ሃይሎች ከትግራይ ማስወጣት እንዲሁም ህጋዊ ያልሆኑ የአማራ አስተዳደሮች ማፍረስ የፌደራል መንግስቱ ሀላፊነት ነው።
— ፕረዝደንት ጌታቸው ረዳ
ፕረዝደንት ጌታቸው ረዳ ከትግራይ ቴሌቭዥን የፕሪቶርያ ስምምነት አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ በነበራቸው ቆይታ ከተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች:—
★ የፕሪቶርያው ስምምነት ቶኩስ የማቆም ስምምነት ነው።
★ የቶክስ ድምፅ እንዲቆም በማድረግ ረገድ ስምምነቱ ስኬታማ ነው።
★ የመሬት ይገበኛል የሚባል እውነት የሚመስል ጥያቄ በሌላኛው ወገን ማለትም በአማራ ክልል ያለ አስመስሎ ማቅረብ ነው፣ እንደ እኔ እምነት ግን የለም የሚል እምነት ነው ያለኝ።
★ የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር “አጨቃጫቂ” ናቸው በሚባሉ የትግራይ ግዝኣቶችን ማስተዳደር የለበትም የሚሉ የፌደራል መንግስቱ ተደራዳሪዎች ነበሩ።
★ የትግራይ ህዝብ ደህንነት እና ህልውና የሚያሰጋ ነገር ከሌለ፣ ከመከላከያ ሃይሉ ውጭ ያሉት ታጣቂዎች እና ወራሪ ሃይሎች ከትግራይ ከወጡ ትጥቅ ተሸክመን የምንኖርበት ምክንያት አይኖርም።
★ የፕሪቶርያው ውል የፈረምነው የትግራይ መሬት አሳልፈን ለመስጠት ሳይሆን በህገ መንግስቱ መሰረት መፈታት አለበት ስለተባለ ነው።
★ ምዕራብ ትግራይ፣ ደቡብ ትግራይ ወደ ነበረበት አስተዳደር መመለስ እንዲሁም ተፈናቃይ ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ ቀደም ብሎ መፈፀም የነበረበት ተግባር ነው የነበረው።
★ የፌደራል መንግስቱ ተፈናቃይ ወገኖችከ ሰኔ 21 2015 ዓ/ም በፊት ወደ ቀያቸው ከመመለስ ቃል ቢገባም አልተፈፀመም።
★ የፕሪቶርያው ውል ሂደት ለማቀላጠፍ ሲባል ከአማራ ክልል አመራሮች ለመስራት ጥረት ቢደረግም የፕሪቶርያው ስምምነት ራሱ መገምገም ፣መደራደር ስለጀመሩ ለማቋረጥ ተገደናል።
★ ሪፈረንደም ለማካሄድ የትግራይ ክልል ምክር ቤት መኖር የግድ ነው። በመሆኑም ግዝያዊ አስተዳደሩ ሪፈረንደም የማካሄድ ህገ መንግስታዊ ሰልጣን የለውም።
★ ግዝያዊ አስተዳደሩ እግር እየጎተተ ነው የሚለው ክስ የተጋነነ ነው።
★ የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲተገበር እና ግጭት ዳግም እንዳያገረሽ ሊሰራ ይገባል።
★ ሁሉንም ልዩነቶቻችን በሰላም መፈታት አለባቸው፣ ከጠብመንጃ ይልቅ ለንግግር እድል መስጠት ይኖርብናል።
★ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዳይተገበር ለሚንቀሳቀሱ አካላት ሁሉ ተቀባይነት የለውም፣ እንታገላቸዋለንም ብለዋል።
ትግራይ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት
ጥቅምቲ 27/2016 ዓ.ም
መቐለ

